Video Editor

Dawit FekadieANYWHERE/REMOTE, ETHIOPIA
Today • Field: Media & Journalism
Employer: Private Company • Full-time • Remote

Scraped from: Afriworket

Ethio truth የዩቲዩብ ቻናል ለሚጀምራቸዉ አዳዲስ እና ነባር ፕሮግራሞች ተጨማሪ ቪዲዮ ኤዲተሮችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። የሥራ መደብ: የቪድዮ ኤዲተር የሥራ ቦታ: የርቀት (Remote) - ባሉበት ቦታ ሆነው የሚሰሩት የሥራ ሰዓት: የሙሉ ጊዜ / በስምምነት ዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶች: የሚዲያውን የጥራት ደረጃ እና ስታንዳርድ የጠበቁ ዕለታዊ መረጃዎችን አቀናብሮ ማዘጋጀት። የቪድዮዎችን ይዘት ይበልጥ ማራኪ ለማድረግ ድምፆችን (Audio Mixing)፣ ጽሑፎችን (Subtitles/Texts) እና አኒሜሽኖችን (Graphics) በተገቢው መንገድ ማካተት። የተሰጡ ስራዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ (Deadline) አጠናቆ ማስረከብ። የሚፈለጉ መስፈርቶች፡ ለስራው የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ቴክኖሎጂ (በቂ አቅም ያለው ኮምፒውተር፣ ስማርት ስልክ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ የኢንተርኔት ግንኙነት ያለዉ / ያላት በ Adobe Premiere Pro, Adobe photoshop, እና በመሳሰሉት) በቂ እውቀት እና የተግባር ልምድ ያለው/ያላት። የዘመኑን የዲጂታል እና የማህበራዊ ሚዲያ አዝማሚያዎችን (Trends) የሚረዳ/የምትረዳ። ኃላፊነት መውሰድ የሚችል/የምትችል እና ያለምንም የቅርብ ክትትል (Remote) በነፃነት እና በብቃት መስራት የሚችል/የምትችል።

Apply