FMCG Field Sales Representative
Scraped from: Afriworket
Job description
We are looking for experienced FMCG Field Sales Representatives to sell and distribute packaged juice across Addis Ababa. Main Role & Responsibilities • Visit retail outlets daily and actively sell our juice products. • Main focus will be neighborhood kiosks/suks, grocery shops and minimarkets. • Approach shop owners, introduce the product, negotiate and close sales. • Find new retail customers within assigned areas. • Follow up with existing shops and generate repeat orders. • Identify areas and shops where the product sells fastest. • Record shops visited, quantities sold, customer contacts and repeat orders. • Coordinate with the delivery vehicle/driver. • Achieve daily and weekly sales targets. Required Skills & Experience • Previous FMCG field sales experience is strongly preferred. • Experience selling beverages, juice, bottled water, soft drinks, dairy, biscuits, snacks or similar FMCG products is highly preferred. • Candidates with previous experience selling directly to kiosks/suks and neighborhood shops are especially preferred. • Good knowledge of Addis Ababa neighborhoods and retail markets. • Existing relationships with shop owners or knowledge of established FMCG sales routes is a major advantage. • Strong communication, negotiation and sales-closing ability. • Energetic, target-oriented and comfortable visiting many shops every day. Education is less important than proven field-sales ability, FMCG experience and knowledge of Addis Ababa’s kiosk/suk market. Compensation & Benefits • Monthly salary is negotiable based on experience and ability. • Attractive sales commission will be provided in addition to the monthly salary. • Strong performers will have the opportunity to earn significantly more through sales commissions and performance incentives. በአዲስ አበባ የታሸገ ጁስ ምርትን ለመሸጥና ለማከፋፈል ልምድ ያላቸው የFMCG የመስክ ሽያጭ ተወካዮች እንፈልጋለን። ዋና የስራ ኃላፊነቶች • በየቀኑ የችርቻሮ መሸጫዎችን በመጎብኘት የጁስ ምርታችንን መሸጥ። • ዋና ትኩረት በየሰፈሩ በሚገኙ ኪዮስኮች/ሱቆች፣ ግሮሰሪዎች እና ሚኒማርኬቶች ላይ ይሆናል። • የሱቅ ባለቤቶችን በቀጥታ በማነጋገር ምርቱን ማስተዋወቅ፣ መደራደር እና ሽያጭ መፈጸም። • በተመደበው አካባቢ አዳዲስ የችርቻሮ ደንበኞችን ማፍራት። • ነባር ደንበኞችን በመከታተል ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ማግኘት። • ምርቱ በፍጥነት የሚሸጥባቸውን ሱቆችና አካባቢዎች መለየት። • የተጎበኙ ሱቆችን፣ የተሸጠ መጠንን፣ የደንበኞችን መረጃ እና ተደጋጋሚ ትዕዛዞችን መመዝገብ። • ከአሽከርካሪውና ከማከፋፈያ ተሽከርካሪው ጋር ተባብሮ መስራት። • የቀንና የሳምንት የሽያጭ ግቦችን ማሳካት። የሚፈለጉ ክህሎቶችና ልምድ • በFMCG የመስክ ሽያጭ ልምድ ያለው/ያላት በጣም ተመራጭ ነው። • በጁስ፣ በለስላሳ መጠጦች፣ በታሸገ ውሃ፣ በወተት ምርቶች፣ በብስኩት፣ በስናክ ወይም በተመሳሳይ FMCG ምርቶች ሽያጭ ልምድ ያለው/ያላት ተመራጭ ነው። • በቀጥታ ለኪዮስኮች/ሱቆች እና ለሰፈር ግሮሰሪዎች የመሸጥ ልምድ ያላቸው እጩዎች በተለይ ተመራጭ ናቸው። • የአዲስ አበባን ሰፈሮችና የችርቻሮ ገበያ በሚገባ የሚያውቅ/የምታውቅ። • ከሱቅ ባለቤቶች ጋር የቀድሞ ግንኙነት ያለው/ያላት ወይም የFMCG የሽያጭ መስመሮችን የሚያውቅ/የምታውቅ ትልቅ ተጨማሪ ጥቅም ነው። • ጥሩ የመግባቢያ፣ የድርድር እና ሽያጭ የመዝጋት ችሎታ። • ታታሪ፣ ንቁ፣ በውጤት ላይ ያተኮረ/ች እና በየቀኑ ብዙ ሱቆችን ለመጎብኘት ዝግጁ የሆነ/ች። ደመወዝ እና ኮሚሽን • ወርሃዊ ደመወዝ እንደ እጩው/እጩዋ ልምድና ችሎታ በድርድር የሚወሰን ይሆናል። • ከወርሃዊ ደመወዝ በተጨማሪ ማራኪ የሽያጭ ኮሚሽን ይኖራል። • ከፍተኛ የሽያጭ ውጤት የሚያስመዘግቡ ሰራተኞች በኮሚሽንና በውጤት ማበረታቻ ተጨማሪ ገቢ የማግኘት ዕድል ይኖራቸዋል።
