Sales and Value Chain Agent
Scraped from: Afriworket
Job description
ሳቢ በማህበረሰብ ደረጃ የሴቶች የእሴት ሰንሰለት አጋሮችን ባሉበት ሆነው በመስራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በኮሚሽን ማሰራት ይፈልጋል። 1. የምግብ ምርቶች ሽያጭ · የሳቢን ምግብ ውጤት ምርቶች ማስተዋወቅና መሸጥ · ደንበኞችንና የአካባቢ መደብሮችን ማፍራት · የደንበኞችን ትዕዛዝ መቀበልና ስርጭትን ማስተባበር · ከደንበኞችና ከቸርቻሪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር 2. የግብርና ግብዓት ማፈላለግ · አርሶ አደሮችንና የአርሶ አደር ቡድኖችን ማግኘት · የግብርና ግብዓት ፍላጎታቸውን መሰብሰብ · ተስማሚ የግብርና ግብዓት አቅራቢዎችን ማፈላለግ · አርሶ አደሮችን፣ አቅራቢዎችንና ሳቢን ማገናኘት · በግብዓት ግዢና ስርጭት ሂደት መሳተፍ ሳቢ የሚያቀርበው · የሽያጭ ማፈላለግ ኮሚሽን · የአፈጻጸም ማበረታቻ · የምርትና የሽያጭ ስልጠና · የገበያና የመስክ ድጋፍ · ሱቅ ካለዎ፣ የራስዎን የደንበኛና ኔትወርክ የመገንባት ዕድል ማን ማመልከት ይችላል? · ቢያንስ ዲፕሎማና ከዛ በላይ የትምህርት ደረጃ በአካባቢዋ ጥሩ የማህበረሰብ ግንኙነት ያላት · በሽያጭ፣ በግብርና፣ በአመጋገብ ወይም በስራ ፈጠራ ላይ የተሰማራች ወይም ፍላጎት ያላት · ጥሩ የመግባባትና የግንኙነት ችሎታ ያላት · ራሷን ችላ መስራት የምትችል · የሽያጭ፣ የችርቻሮ፣ የግብርና ወይም የማህበረሰብ ሥራ ልምድ ካላት ተመራጭ ነው የሥራ ቦታ አዲስ አበባ አካባቢና ዋና ዋና ከተሞች ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የሚኖሩበትን አካባቢ እና አጭር የሥራ ልምድ በዚህ ፎርም https://forms.gle/4EdXopP4gVfCQojb7 በመሙላት ይላኩ።
