Senior Sales & Marketing officer
Scraped from: Afriworket
Job description
የኪም ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን (የአማሄ ማኑፋክቸሪንግ እህት ኩባንያ) በማርኬቲንግ ኤጀንሲ፣ በፕሮሞሽን እና በንግድ ማስተዋወቅ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ልምድ እና ብቃት ያለውን ተወዳዳሪ በ ሲኒየር የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ሥራ (Senior Sales & Marketing ) የሥራ መደብ ላይ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ዋና ዋና ኃላፊነቶች (Key Responsibilities) • የስትራቴጂ ዝግጅት: የማርኬቲንግ ኤጀንሲውን አጠቃላይ የሽያጭ እና የፕሮሞሽን ስትራቴጂ መንደፍ፣ አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን ማወቅ እና ተግባራዊ ማድረግ። • የደንበኞች ግንኙነት እና የገበያ : ከአምራች ኩባንያዎች፣ ከድርጅቶች እና ከትልልቅ ደንበኞች ጋር የንግድ ግንኙነት መፍጠር፣ ኮንትራቶችን መደራደር እና የረጅም ጊዜ አጋርነት መመሥረት። • የቡድን መሪነት: የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ቡድኑን በበላይነት መምራት፣ የሥራ ዕቅድ መስጠት፣ አፈጻጸምን መከታተል እና ማብቃት። • የዘመቻዎች (Campaigns) አስተዳደር: የዲጂታል እና ሜዳ ላይ (BTL/ATL) የፕሮሞሽን ሥራዎችን፣ የሕዝብ ግንኙነት እና የማስተዋወቅ ዘመቻዎችን በበላይነት ማቀድ እና መከታተል። • የገበያ ጥናት: የኢንዱስትሪውን እንቅስቃሴ፣ የተወዳዳሪዎችን ሁኔታ እና የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የገበያ ጥናት ማካሄድ እና የንግድ ዕድገት ማስመዝገብ። • የሥራ ልምድ: • ለባችለር ዲግሪ ከ2 ዓመት በላይ የሥራ ልምድ ያላት። • በ ማርኬቲንግ ኤጀንሲ፣ በፕሮሞሽን ወይም በማስታወቂያ ኩባንያዎች ውስጥ በኃላፊነት ደረጃ የሰራ/ች ቢሆን ይመረጣል።
