Site Engineer
Scraped from: Afriworket
Job description
የቀጣሪ ድርጅት ስም ጌት ሃብ እንጨት ፣ ብረትና አልሙኒየም ስራዎች ድርጅት የስራ መደቡ የሳይት ኢንጅነር(Site Engineer) የስራ ኃላፊነቶችና ተግባሮች • ድርጅቱ በሳይት ላይ የሚሰሩትን ማንኛዉንም የልኬትና የገጠማ ስራዎች እቅድ በማዉጣት ይሰራል/ትሰራለች፣ • የሚገጠሙ ማንኛዉም ምርቶች በደንበኛ ፍላጎት በተሰራዉ ዲዛይን መሰረት እንዲሰራ የማድረግ፣ • ድርጅቱ በሳይት እንዲሰሩ የመደባቸዉን ሰራተኞች በድርጅቱ የስራ ሰዓት በማክበር እንዲሰሩ የማድረግ፣ • ሳይት ላይ ሊገጠሙ ከወርክ ሾፕ የሚላኩ ምርቶች በዲዛይኑና በከቲንግ ሊስቱ መሰረት አልቆለት መምጣቱን በማረጋገጥ እና በገጠማ ስራ ላይ ጥራት(Quality Control) መቆጣጠርና የጥራት ደረጃዎች ተጠብቆ መሰራቱን በማረጋገጥ የመስራት፣ • የድርጅቱ ስራ ደህንነት(Health & Safety) መመሪያዎችን ተከብረዉ እንዲሰሩ በሳይት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የመስራት፣ • ድርጅቱ በሚሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ማንኛዉንም አይነት ምርቶች አሰርቶ በሳይት ላይ ለማስገጠምለሚፈልጉ ደንበኞች በፍላጎታቸዉ መሰረት የሳይት ልኬት በትክክል ለክቶ ለዲዛይነር ሰራተኛ የሳይት መለኪያ(Site Measurement) ፈርሞ በማስረከብ ይሰራል፣ በገጠማ ወቅትም ችግር እንዳይኖረዉ ልኬቱና ዲዛይኑ ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ በኃላፊነት ይሰራል፣ • ለሳይት ገጠማ ስራ የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችንና የሰዉ ኃይል ከሚሰራዉ ስራ ጋር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በወቅቱ ለምርት ክፍል ኃላፊ በማሳወቅና እንዲፈጸምለት በመጠየቅ በእቅድ ምርቶች እንዲገጠሙና ለደንበኛዉ እንዲደርስ የማስረግ ስራ ይሰራል፣ • በሳይት ላይ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ዝርዝር የስራ አፈጻጸም ዕለታዊና ሳምንታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ሪፖርት በማቅረብ ይሰራል/ትሰራለች፣ • በሳይት ላይ ለሚፈጠሩ የቴክኒክ ችግሮችን በመለየትና ፈጣን መፍትሔ መስጠት ይሰራል፣ • ድርጅቱ በሚሰጠዉ ዉክልና መሰረት በሳይት ለሚሰሩ ስራዎች ከደንበኛ፣ ከኮንሰልታንት፣ባለቤቶችና ከፕሮጀክት አስተዳዳሪ ጋር በቅርበት በመሆን ይሰራል • የሳይት የገጠማ ስራዎች የስራ መርሃ ግብር(Work Schedule) በማዉጣትና ጥብቅ ክትትል በማድረግ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሰረት መፈጸሙን እለት በእለት በማረጋገጥ ይሰራል፣ • ሳይት ላይ የሚሰሩ ማንኛዉም ስራዎች ላይ በደንበኛዉ ፍላጎት መሰረት የሥራ ለውጦች(Variation Orders) ሲኖር መመዝገብና ልቅርብ ኃላፊ በወቅቱ በማሳወቅ ተገቢዉ መፍትሔ እንዲሰጥበት በመከታተል ይሰራል፣ • ከወርክ ሾፕ ወደ ሳይት የተጓጓዙ ምርቶች በትክክል በታለመለት ሳይት ላይ መድረሳቸዉን እና ለታለመለት ስራ ብቻ የመጡ መሆኑን በማረጋገጥ ይሰራል፣ • የስራ ሂደት ፎቶዎችንና ሌሎች መረጃዎችን መዝገቦችን መያዝ፣ • በሳይት ላይ ተሰርተዉ የተጠናቀቁ ምርቶች በትክክለ ስለመሰራታቸዉ የመጨረሻ ምርመራ(Final Inspection) ማካሄድና ጉድለት ያለባቸዉን በዝርዝር በመለየት በወቅቱ እንዲስተካከሉ በማድረግ ይሰራል እንዲሰራም ያሳዉቃል፣ • የገጠማ ስራዉ ሙሉ ለሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ የደንበኛ ርክክብ ሰነዶችን በማዘጋጀት ርክክብ እንዲደረግ ያደርጋል፣ • የድርጅቱ የስራ መስሪያ ማሽኖችና ጥሬ እቃዎች ብክነት እንዳይኖር በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሰረት እንዲሰራ ክትትል በማድረግ ይሰራል እንዲሁም የሰራተኛ አፈጻጸም በመገምገም ሪፖርት ያቀርባል፣ • ከድርጅቱ ዲዛይን ፣ ምርት(Production)፣ ግዥ(Procurement) ክፍሎች እና ሌሎች ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር ተቀናጅቶና ተግባብቶ ይሰራል፣ • በምርቱ ወይም በሰራተኞች ዲዚፕሊን እንዲሁም በሌሎች መሰል ድርጊቶች ጥፋት እንዳይኖር ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ይሰራል ይሁን እንጂ ይህም እንዳለ የደንበኛ ቅሬታዎችን በሚያቀርብበት ጊዜ በወቅቱ በሙያዊ ዲሲፕሊን ሁኔታዉን በመረዳት መፍተሄ እዲሰት ያደርጋል ከዚያ በላይ ከሆነ ለቅርብ ኃላፊ በወቅቱ በማሳወቅ ይሰራል፣ • ለድርጅቱን ደንብና መመሪያ አክብሮ የመስራት፣ የስራ ሂደቶችና የጥራት መመሪያዎች ተገዢ ሆኖ በኃላፊነት መስራት፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች መስፈርቶች • ጥሩ የደንበኛ አያያዝ ችሎታ ያለዉ፣ • በቀላሉ የመግባባት ችሎታ ያለዉ • ጥሩ ስነ ምግባር ያለዉ • የድርጅቱን ሚስጥር ጠባቂ የሆነ • የድርጅቱን ደንብና መመሪያ አክብሮ መስራት የሚችል • ከዚህ በፊት በሳይት ኢንጅነሪንግ ከ2 ዓመት በላይ የሰራ/የሰራች፣ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች • የትምህርት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ • የፋይዳ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ • CV • የስራ ልምድ ፎቶ ኮፒ ብዛት • አንድ(1) ጾታ • ሴት/ወንድ ክፍያ • ወርሃዊ ደመወዝ ሆኖ በስምምነት አድራሻ • ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ሮቤራ ካፌ አጠገብ ለበለጠ መረጃ 0911661672 መደወል ይቻላል
