
Vehicle Movement Controller/ Yard Marshall
Scraped from: HaHu Jobs
Job description
ቲቪኢቲ ደረጃ 1 በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ቀች አግባብነት ካለው የስራ ልምድ ጋር ዋና ዋና ኃላፊነቶች - የጭነት መኪኖችና ኮንቴነሮች የደንበኞችን የአካባቢ፣ ጤናና ደህንነት መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን መመርመር - ለአሽከርካሪዎችና ለረዳት ሠራተኞች የግቢውንና የጭነት መጫኛ ደንቦች ማስረዳትና አፈጻጸማቸውን መከታተል የጭነት ማጓጓዣ ቡድን አባላት አስፈላጊውን የግል መከላከያ መሣሪያ መያዛቸውንና በአግባቡ መጠቀማቸውን ማረጋገጥ - የጭነት መኪኖቹ የጎማ ማቆሚያ፣ የኋላ ማስጠንቀቂያ ድምፅ እና ሌሎች አስፈላጊ የደህንነት መሣሪያዎች ያሏቸውና በአግባቡ የሚሠሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ - በግቢው ውስጥ የሚፈቀዱ የጥገና ሥራዎች ከመከናወናቸው በፊት የአደጋ ስጋት ግምገማ ማካሄድ - በግቢው ውስጥ የሚከሰቱ የአካባቢ፣ ጤናና ደህንነት ደንብ ጥሰቶችንና አደጋዎችን ለሚመለከተው ቡድን በወቅቱ ማሳወቅ - የግቢውን ቦታ በከፍተኛ ደረጃና በደህንነት ለመጠቀም፣ የጭነት መኪኖች በሥርዓት እንዲቆሙና እንዲደራጁ ማድረግ - የመኪና ማቆሚያ ደንቦች፣ ለምሳሌ የጎማ ማቆሚያ መጠቀም፣ ሞተር ማጥፋትና አሽከርካሪዎች በተመደበው የማረፊያ ቦታ መቆየታቸውን ማስፈጸም - የግቢውን መደበኛ የአሠራር ሂደቶች ፣ የእግረኞች መንገድ፣ የማጨሻ ቦታና የPPE አጠቃቀም ደንቦች መከበራቸውን ማረጋገጥ
